የግላዊ ጉዳይ ጥበቃ ፖሊሲ
ጥረታችን/ኃላፊነታችን
ሚኒስቴራችን በዚህ ፖርታል ላይ በሚደረግ የመረጃ ቅብብል ወቅት ለሚሰጡት የግል መረጃ በጥንቃቄ ይይዛል፡፡ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸውን የግል መረጃዎትን የመጠበቅ ኃለፊነታችንን በመገንዘብም ይህንን የግለኝነት መብት ፖሊሲና ደህንነት ገፅ አዘጋጅተናል፡፡
ይህንን ፖርታል ለጉብኝት ወይም ለኤሌክትሮኒክ-ግብይት በሚጠቀሙበት ወቅት ለሚሰጡት የግል መረጃ ተገቢውን ጥበቃ ለማድረግ የላቀ ጥረት እናደርጋለን፡፡
መረጃዎትን መውሰድና መጠቀም
ድህረ ገፃችን በሚጎበኙበት ወቅት፤ አገልግሎቱን ለማግኘት ከሚጠየቁ መረጃዎች በስተቀር የግል መረጃዎትን እንዲሰጡ አንጠይቅም፡፡
የአይ.ፒ አድራሻ መውሰድ
የመረጃ ድረ-ገፃችን በሚጎበኙበት ቅፅበት የድረ-ገፅ ሰርቨራችን የእርስዎን አይ.ፒ አድራሻ ይሰበስባል (የእርስዎ የአይ.ፒ አድራሻ የኮምፒውተርዎት ልዩ ቁጥር ሲሆን ኢንተርኔት ላይ የሚገኙ ሌሎች ኮምፒውተሮች ለእርስዎ መረጃ የሚልኩበት አድራሻ ነው፡፡) የእርስዎን የአይ.ፒ አድራሻ ከሰርቨራችን በኩል ለሚከሰቱ ችግሮች ለመፍታትና የድረ-ገፃችንን የተጠቃሚ ብዛት መረጃ ለማጠናቀር እንጠቀምበታለን፡፡
የኩኪዎች አጠቃቀም
አንዳንድ የመንግስት ድረ-ገጾች ኩኪዎችን ይጠቀማሉ። ኩኪዎች በአጠቃላይ ተጠቃሚዎች በድረ-ገጾቻችን ላይ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ ይጠቀማሉ። ከመረጡ፣ የይለፍ ቃልዎን ለ'ማስታወስ' እና ወደ አንዳንድ ጣቢያዎች መግባት ቀላል እና ፈጣን እንዲሆን ለማድረግ ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ።
ለግል መረጃዎት የሚደረግ ጥበቃ
የግል መረጃዎት እንዲያውቁት ከሚፈለግ የመንግስት ሰራተኞች በስተቀር ለማንም ግልፅ አይደረግም፡፡
ጠቃሚ ማሳሰቢያ
ከድረ-ገጾቻችን አንዳንዶቹ በሌሎች የህዝብ እና/ወይም የግል ዘርፍ ድርጅቶች የተፈጠሩ እና የሚጠበቁ ሌሎች ጣቢያዎችን ያገናኛሉ። እነዚህን አገናኞች ለእርስዎ መረጃ እና ምቾት ብቻ እናቀርባለን። ወደ ውጭ ድረ-ገጽ ሲገናኙ፣ የእኛን ፖርታል እየለቀቁ ነው እና የእኛ የመረጃ አያያዝ ፖሊሲዎች ከዚህ በኋላ ተፈጻሚ አይሆኑም።